Previous Next

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

የኮምፓሽን አገልግሎት በህብረት አምባ ET100 ፕሮጀክት የኮምፓሽን ኢትዮጵያ የመጀመሪያው ፕሮጀክት ነው፡፡ ይህ አገልግሎት እድሜያቸው ከ3 እስከ 22 ዓመት የሆኑ ልጆችን እና ወላጆቻቸውን በጥናት እና በመረጃ በተደገፈ መንገድ በሁለንተናው አገልግሎት በመርዳት፣ በማስተማር ልጆችን እና ቤተሰቦቻቸውን የእግዚአብሄርን መንግስት ወንጌል እንዲሰሙ ባለው እድል ሁሉ ይተጋል፡፡

ኮምፓሽን አገልግሎት የሚከተሉትን ንዑስ ዘርፎች የያዘ ነው፡፡

1. የትምህርት ዘርፍ

2. አካላዊ ዘርፍ

3. የማህበራዊ ዘርፍ

4. መንፈሳዊ ዘርፍ

 

5. አስተዳራዊ ዘርፍ

በዚህ አገልግሎቱም ባለፉት ዓመታት ብዙ ህጻናትን በወንጌል በመድረስ እግዚአብሄር በህይወታቸው ከብሮ እንዲታይ ምክንያት የሆነ አገልግሎት ነው፡፡

Previous Next

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

“ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”

ማቴ. 28:18-20

 

የወንጌል ስርጭት አገልግሎት የእግዚአብሄርን መንግስት ወንጌል በከተማም በገጠርም በመስበክ እና አማኞች የዚህ ወንጌል ምስክሮች እንዲሆኑ የሚያስተባብር አገልግሎት ነው፡፡ ሕብረት አምባ ላለፉት ረጅም አመታት በአዲስ አበባም ሆነ በገጠሩ የአገራችን ክፍሎች የወንጌል ሚሽነሪዎችን በመላክ እጅግ ብዙ አጥቢያ አብያተክርስቲያናት እንዲተከሉ ምክንያት ሆናለች፡፡ 

ዛሬም ቤተክርስቲያኒቱ ዋና ትኩረቷን ወንጌል አድርጋ አማኞችን የወንጌል ማህበርተኞች በማድረግ ባላቸው ነገር ሁሉ የወንጌል ተሳታፊዎች እንዲሆኑ በማስተባበር ላይ ትገኛለች፡፡

ይህንን አገልግሎት ለመደገፍ የምትሹ በቤተክርስቲያኒቱ አካውንት ልባችሁ ያሰበውን በማስገባት እናንተም የወንጌል ማህበርተኛ እንድትሆኑ የአገልግሎት ክፍሉ ያበረታታል፡፡

"መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።" የሐዋ. 4:12

Previous Next

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive











 

ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል። የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” 2ኛ ጢሞ.3:14-17

 

የልጆችና ወጣቶች አገልግሎት የልጆችን የሰንበት ትምህርት ከማስተባበር ጀምሮ የተተኪ ወጣት አገልጋዮችን አገልግሎት እስከመምራት ድረስ የሚዘልቅ ሰፊ አገልግሎት ነው፡፡

በአገልግሎት ክፍሉ ስር የልጆች አገልግሎት በቤተክርስቲያናችን ያሉ ልጆች ከልጅነታቸው ጀምሮ በእግዚአብሄር ቃል እውቀት ታንጸው እንዲያድጉ በትጋት ያገለግላል፡፡ የክረምት ትምህርት በማዘጋጀት ልጆች አልባሌ ቦታ እንዳይውሉ በቃሉ በመኮትኮት መንፈሳዊ ህይወታቸውን ይገነባል፡፡

የወጣቶች አገልግሎት ደግሞ የቤተክርስቲያናችን ወጣቶች ትኩስ እድሜያቸውን ለጌታ ሰጥተው በቃሉ እውነት ራሳቸውን እንዲያንጹ፣ በህብረት እንዲተጉ እና የቤተክርስቲያንን አገልግሎት ተረክበው መምራት እንዲችሉ ከጎናቸው በመቆም ያግዛል፤ ያስተባብራል፡፡ 

Previous Next

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ይህ የአገልግሎት ክፍል በቤተክርስቲያን ያሉ ትምህርቶች መጽሃፍቅዱሳዊነት ይዘታቸውን ይዘው እንዲቀጥሉ ይከታተላል፡፡ አባላት ከተጠመቁ በኋላ የጌታን ተከተል ትምህርት፣ የማስተር ላይፍ ትምህርትከዚያም የአገልግሎት ትምህርት ተምረው ወደመረጡት የአገልግሎት ክፍል ገብተው እንዲያገለግሉ ይመራል፤ ያስተባበራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከሌሎች የአገልግሎት ፍሎች ጋር በመቀናጀት ክፍሎች የሚያስፈልጋቸውን ስልጠናዎች በማዕከል ያዘጋጃል፡፡

ሕብረት አምባ

 

 

ለ50 ዓመታት የዘለቀ የእግዚአብሄርን መንግስት ወንጌል የማድረስ እና ያመኑትን ደቀመዛሙርት የማድረግ አገልግሎት

 

©2024 Hibret Amba Kalhiwot Church. All Rights Reserved.

Search