"ያመኑትም ሁሉ አብረው ነበሩ፤ ያላቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ፥ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉት ነበር። በየቀኑም በአንድ ልብ ሆነው በመቅደስ እየተጉ በቤታቸውም እንጀራ እየቈረሱ፥ በደስታና በጥሩ ልብ ምግባቸውን ይመገቡ ነበር" የሃዋርያት ስራ 2:44-46
አገልግሎቱ የእግዚአብሄርን ቃል መሰረት በማድረግ አማኞች በየአካባቢያቸው ባሉ ህብረቶች ተይዘው ከሌሎች አማኞች ጋር የእግዚአብሄርን ቃል በመካፈል፣ በህብረት እንዲሁም ባላቸው መንፈሳዊም ሆነ ቁሳዊ ነገር በመካፈል እንዲተጉ የሚያግዝ አገልግሎት ነው፡፡