Previous Next

የልጆችና ወጣቶች አገልግሎት

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive
 











 

ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል። የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” 2ኛ ጢሞ.3:14-17

 

የልጆችና ወጣቶች አገልግሎት የልጆችን የሰንበት ትምህርት ከማስተባበር ጀምሮ የተተኪ ወጣት አገልጋዮችን አገልግሎት እስከመምራት ድረስ የሚዘልቅ ሰፊ አገልግሎት ነው፡፡

በአገልግሎት ክፍሉ ስር የልጆች አገልግሎት በቤተክርስቲያናችን ያሉ ልጆች ከልጅነታቸው ጀምሮ በእግዚአብሄር ቃል እውቀት ታንጸው እንዲያድጉ በትጋት ያገለግላል፡፡ የክረምት ትምህርት በማዘጋጀት ልጆች አልባሌ ቦታ እንዳይውሉ በቃሉ በመኮትኮት መንፈሳዊ ህይወታቸውን ይገነባል፡፡

የወጣቶች አገልግሎት ደግሞ የቤተክርስቲያናችን ወጣቶች ትኩስ እድሜያቸውን ለጌታ ሰጥተው በቃሉ እውነት ራሳቸውን እንዲያንጹ፣ በህብረት እንዲተጉ እና የቤተክርስቲያንን አገልግሎት ተረክበው መምራት እንዲችሉ ከጎናቸው በመቆም ያግዛል፤ ያስተባብራል፡፡ 

ሕብረት አምባ

 

 

ለ50 ዓመታት የዘለቀ የእግዚአብሄርን መንግስት ወንጌል የማድረስ እና ያመኑትን ደቀመዛሙርት የማድረግ አገልግሎት

 

©2024 Hibret Amba Kalhiwot Church. All Rights Reserved.

Search