ቀድሞ የወጣት ማዕከል በመባል ትታወቅ የነበረችው የዛሬዋ ህብረት ቃለህይወት ቤተክርስቲያን አመሰራረቷ እና ዕድገቷ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን እና በአካባቢው ያሉ የትምህርት ተቋማትን ማዕከል ባደረገ መልኩ ነው፡፡
ወንጌሉን በአካባቢዋ በማስፋፋትና ብዙዎችን ከተለያዩ እስራት ወጥተው በእግዚአብሄር መንግስት ባለው ነጻነት እንዲገቡ በማድረግ የድርሻዋን ስትወጣ የኖረችው ቤተክርስቲያናችን ዛሬም በእግዚአብሄር ምሪት እና በመንፈሱ ሃይል በመንቀሳቀስ የታላቁን ተልዕኮ ማለትም ወንጌልን ለአለም ሁሉ መስበክን እና ደቀመዛሙርት ማድረግን ተልዕኮዋ አድርጋ ትንቀሳቀሳለች፡፡