525 የህንጻ ግንባታ ሂደት

Project 525

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive
 

 

ለዚህ የታደለ ትውልድ ሠላም ይሁን!

 

ቤተክርስቲያናችን ለብዙ ዓመታት ስትጸልይበት እና ስትቃትትበት የነበረውን የማምለኪያ ቦታ ጥያቄ እንደእግዚአብሄር ፈቃድ በ2012 ዓ.ም የቦታ ማረጋገጫ ካርታ በመቀበል ቦው በእጃችን እንዲገባ ስላደረገ እግዚአብሄርን ከልብ እናመሰግናለን፡፡ የቱንም ያህል ጠላት የእግዚአብሄርን ሃሳብ ለማበላሸት ቢጥርም ድል የአምላካችን በመሆኑ ዛሬ የዲዛይን ጥናቱን አስጠንተን ዋናውን የግበ,ንባታ ሥራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡

 

ይህ ቦታ በእጃችን እንዲገባ ብዙዎቻችሁ ጸልያችኋል፤ አልቅሳችኋል፤ በተለያዩ የመንግስት አካላት ቢሮዎች በአካል በመሄድ ጉዳዩን ለማስጨረስ ጥራችኋል፡፡ በገንዘብና በአሳብ ከቤተክርስቲያን ጎን ቆማችኋል፡፡ የማንንም ሰው ድካም ከንቱ የማያደርገው ጌታ ዋጋችሁን ይክፈላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡

 

ይህ ቦታ በብዙ ምጥ እና ጸሎት እንደመገኘቱ መጠን በቀጣይም ለሚሰራው ታላቅ ስራ ብዙ ጸሎት፣ ብዙ ምክክር፣ እንዲሁም ከመቼውም ጊዜ ይልቅ የልብ አንድነት እና ቅንጅት የሚያስፈልግበት ወሳኝ ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡ እግዚአብሄር ሥራውን የሚሰሩለት ዕውቀትና ገንዘብ ያላቸው በርካታ ሰዎች እያሉት በዚህ ዘመን፣ በዚህ ጊዜ፣ ይህን ታላቅ ሥራ በእጃችን ላይ ለ,ስላኖረው በእጅጉ ልናመሰግነው ይገባል፡፡

 

ይህ በሰው ፍላጎትና መሻት የሚሰጥ እድል አይደለም፡፡ እንደምናውቀው ዳዊት የእግዚአብሄርን ቤት ለመሥራት እጅግ ጓጉቶ ሳለ እግዚአብሄር ግን ንጉሱ ዳዊት ሳይሆን ልጁ ሰለሞን ቤቱን እንዲሰራለት እንደመረጠው ዛሬም እኛ ስለፈለግን ሳይሆን እግዚአብሄር ስራውን እንድንሰራለት ዕድለኞች አድርጎናልና በብዙ ትህትና ጌታን ልናመሰግነው፣ ለሥራውም እጃችንን ልናበረታ ይገባል፡፡

 

ወገኖች ሆይ፡ እግዚአብሄር ለሚመለክበት፣ ነፍሳት ለሚድኑበት፣ ልጆቻችን የሠንበት ትምህርት ለሚማሩበት እና በርካታ አገልግሎት ለሚሰጠው ለዚህ የህንጻው ሥራ ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ተገምቷል፡፡ የእግዚአብሄር ገንዘቡ ህዝቡ ስለሆነ (ሚልክ.3፡1) ሁላችንም ቤቱን እንድንሰራለት ጌታ የሰጠንን ታላቅ እድል አውቀንና ተረድተን ገንዘባችንን፣ ዕውቀታችንን፣ ማሽነሪዎቻችንን፣ ጉልበታችንን እንዲሁም ሁሉ ነገራችንን ቅዱስ መሥዋዕት አድርገን በማቅረብ ቤቱን እጅ ለእጅ ተያይዘን እንድንሠራ በ525 ግንባታ ኮሚቴ ስም ጥሪዬን በአክብሮት አስተላልፋለሁ፡፡

 

 

 

ሙሉጌታ አሃዱ

 

የህንጻ ግንባታ ኮሚቴ ሰብሳቢ

 

 

 

ሕብረት አምባ

 

 

ለ50 ዓመታት የዘለቀ የእግዚአብሄርን መንግስት ወንጌል የማድረስ እና ያመኑትን ደቀመዛሙርት የማድረግ አገልግሎት

 

©2024 Hibret Amba Kalhiwot Church. All Rights Reserved.

Search