ይህ የአገልግሎት ክፍል በቤተክርስቲያን ያሉ ትምህርቶች መጽሃፍቅዱሳዊነት ይዘታቸውን ይዘው እንዲቀጥሉ ይከታተላል፡፡ አባላት ከተጠመቁ በኋላ የጌታን ተከተል ትምህርት፣ የማስተር ላይፍ ትምህርት፣ ከዚያም የአገልግሎት ትምህርት ተምረው ወደመረጡት የአገልግሎት ክፍል ገብተው እንዲያገለግሉ ይመራል፤ ያስተባበራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከሌሎች የአገልግሎት ክፍሎች ጋር በመቀናጀት ክፍሎች የሚያስፈልጋቸውን ስልጠናዎች በማዕከል ያዘጋጃል፡፡