የወንጌል ስርጭት አገልግሎት

Previous Next

የምስክርነት፣ ደቀመዛሙርት የማድረግ እና የቤተክርስቲያን ተከላ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive
 

“ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”

ማቴ. 28:18-20

 

የወንጌል ስርጭት አገልግሎት የእግዚአብሄርን መንግስት ወንጌል በከተማም በገጠርም በመስበክ እና አማኞች የዚህ ወንጌል ምስክሮች እንዲሆኑ የሚያስተባብር አገልግሎት ነው፡፡ ሕብረት አምባ ላለፉት ረጅም አመታት በአዲስ አበባም ሆነ በገጠሩ የአገራችን ክፍሎች የወንጌል ሚሽነሪዎችን በመላክ እጅግ ብዙ አጥቢያ አብያተክርስቲያናት እንዲተከሉ ምክንያት ሆናለች፡፡ 

ዛሬም ቤተክርስቲያኒቱ ዋና ትኩረቷን ወንጌል አድርጋ አማኞችን የወንጌል ማህበርተኞች በማድረግ ባላቸው ነገር ሁሉ የወንጌል ተሳታፊዎች እንዲሆኑ በማስተባበር ላይ ትገኛለች፡፡

ይህንን አገልግሎት ለመደገፍ የምትሹ በቤተክርስቲያኒቱ አካውንት ልባችሁ ያሰበውን በማስገባት እናንተም የወንጌል ማህበርተኛ እንድትሆኑ የአገልግሎት ክፍሉ ያበረታታል፡፡

"መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።" የሐዋ. 4:12

ሕብረት አምባ

 

 

ለ50 ዓመታት የዘለቀ የእግዚአብሄርን መንግስት ወንጌል የማድረስ እና ያመኑትን ደቀመዛሙርት የማድረግ አገልግሎት

 

©2024 Hibret Amba Kalhiwot Church. All Rights Reserved.

Search