የወንጌል ሥርጭት
ወንጌልን በአዲስ አበባና በገጠር ከተሞች ማሠራጨት
ደቀመዝሙር ማድረግ
ያመኑትን የጌታን መንገድ በማሳየትና በማስተማር የጸኑ ደቀመዛሙርት ማድረግ
ሁለንተናዊ አገልግሎት
በአካባቢያችን ያለውን ማህበረሰብ በሁለንተናዊ መንገድ ማገልገል
እንኳን ወደ ሕብረት አምባ ቤተክርስቲያን በደህና መጡ!
ህብረት አምባ ቃለህይወት ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለከተማ አራት ኪሎና ፒያሳ መካከል በሚገኘው የናዝሬት ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ትገኛለች፡፡ ቤተክርስቲያናችን ላለፉት 50 ዓመታት ወጣቶችን እና ሌሎችንም የህብረተሰብ ክፍሎች በወንጌል በመድረስ፣ ደቀመዛሙርት በማድረግና ለእግዚአብሄር መንግስት ሥራ በማሰማራት ውጤታማ አገልግሎትን ስትፈጽም ኖራለች፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ታሪክ ታላቅ የተሃድሶ እንቅስቃሴ ከታዩባቸው አጥቢያዎች ውስጥ ተጠቃሽ ሆና ትገኛለች፡፡
በማህበረሰባዊ አገልግሎትም ውስጥ የኮምፓሽን አገልግሎት የመጀመሪያው ፕሮጀክት ET100 የተጀመረባት ቤተክርስቲያን ናት፡፡ ከዚህ አልፎም በአካባቢው ያለውን ማህበረሰብ በተለያዩ መንገዶች በመርዳትና በማገዝ የእግዚአብሄርን ፍቅር ስታካፍል ኖራለች፡፡
ክብር ሁሉ ለእግዚአብሄር ይሁን፡፡
Project 525
የህንጻ ግንባታ ኮሚቴው ጌታ ኢየሱስ 5 እንጀራ እና 2 ዓሣ ለ5000 ሰዎች የመገበበትን ተዓምር እንደመነሻ በማድረግ 525 የግንባታ ኮሚቴ በማለት ይጠራል፡፡
እግዚአብሄር አምላክ በተዓምራቱ የሰጠንን ይህንን ቦታ ለከተማዋ በሚመጥን እንዲሁም እግዚአብሄርን በሚያከብር መልኩ የተዘጋጀ ህንጻ ለመስራት የዲዛይን ስራው አልቆ የመሠረት ድንጋይ ለመጣል በዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡
አማኞች ሁሉ፣ በዚህች ቤተክርስቲያን በተለያየ መልኩ የተጠቀማችሁ ወገኖች በሙሉ ለዚህ ስራ እጃችሁን እንድትዘረጉ በጌታ ፍቅር እንጠይቃለን፡፡
በዚህ የህንጻ ግንባታ ቤተክርስቲያንን ለማገዝ የምትፈልጉ ሁሉ በሚከተለው የባንክ አካውንት ቁጥር በልባችሁ ያለውን ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
እግዚአብሄር ይባርካችሁ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ 1000004540496
ብርሃን ባንክ፡ 1600550009820
Join our programs every Tuesday, Friday and Sunday.
Tuesdays: Healing and Deliverance Ministry
Wednesdays: Sisters' Ministry
Fridays: Youth Service
Sundays: Regular Worship and Fellowship Day
Wednesdays: Sisters' Ministry
Fridays: Youth Service
Sundays: Regular Worship and Fellowship Day
ማክሰኞ፡ የፈውስ እና ነጻ የማውጣት ቀን
ረቡዕ: የእህቶች ፕሮግራም
ረቡዕ: የእህቶች ፕሮግራም
አርብ፡ የወጣቶች ፕሮግራም
እሁድ፡ ቋሚ የአምልኮ እና የህብረት ቀን